የአንደኛ አመት ተማርዎች የካፌው የምግብ አያያዝ መስተካከል አለበት ሲሉ ቅሬታ
አቀረቡ፡፡
በተለይም ቅሬታቸው ሚያተኩረው በካፌው ምግብ አያያዝ ላይ ሲሆን
ከምግቡ ንጽህና አንስቶ ትራፌዎቹን አወጋገድ ላይ ቅራታ
አለን ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ በተለይም ተማሪው የተገለገለበትን ኩባያ እና መመገቢያ ሰሀን በአግባቡ ወደቦታው ስለማያደርሰው መዝረክረክ
እና ለአይን የማይመች ሆኖ እንደአገኙት ገልጸዋል፡፡
ተማሪዎቹ እንደገለፁት በተለይ ችግሩ የሚስተዋለው በካፌ
አዳራሾች ውስጥ ጠበቅ የለ ቁጥጥር ባለመኖሩ ነው የሚል አስተያየታቸውን ገልፀዋል፡፡
የነጋገርናቸው የካፌ ሰራተኞች በበኩላቸው እንደተናገሩት ተማሪው ከተመገበ በሃላ የተመገበበትን
ሰሀን በአግባቡ ወደ ቦታው ስለማይመልስ ቀጣይ ለመመገብ የሚገባው ተማሪ እንደሚቸገር እና ተማርው እየተመገበ የፅዳት አገልግሎት ስለማይሰጥ ተማሪው ተመግቦ እስኪጨርስ ለመጠበቅ እንደሚገደዱ አስታውቀዋል፡፡
No comments:
Post a Comment