በግቢ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ክለባት ድጋፍ ጠየቁ፡፡
በአካዳሚውም ሆነ በመዝናኛው ዘርፍ ተዋቅረው የሚንቀሳቀሱት እነዚህ ክለባት ከ 10 በላይ
ሲሆኑ ተከታታይ የሆነ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ስለማያገኙ የአቅም መዳከም እንደተከሰተባቸው ገልጸዋል፡፡ አብዛኞቹ ክለባት የሚንቀሳቀሱት በአባላቱ
ድጎማ ሲሆን ድጎማው በተለያዮ ምክንያቶች በመቋረጡ በአብዛኞቹ ክለባት ህልውና በአደጋ ላይ
እንደሚገኝ የክለባት ተጠሪዎች ገልጸዋል፡፡
በተማሪ ህብረት የክለባት ተጠሪ የሆነው ተማሪ ገብረ መድህን እንደገለጸው በፋይናስ እጥረት ምክንያት ህጋዊ ለሆኑት ክለባት ይሰጥ የነበረው የገንዘብ ድጎማ እንደተቋረጠ እና ችግሩ ሲፈታ የሚሰጠውን ድጋፍ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡ በተያያዘ ተጠሪው አንደተናገረው እነዚህ ክለባት ተማሪው ያለውን ተዕስጧእንዲያወጣ እንዲሁም እንዲተቀምበት ከማድረግ አንፃር ከፍተኛ ተግዳሮት እንዳላቸው አስታውሶ ተማሪው በግቢ ቆይታው ልምድ የሚለዋወጥበት እና የሚማማርበት ነው ሲል መልዕክቱን አስተላልፎአል
No comments:
Post a Comment