ባሳለፍነው ሳምንት በአሜሪካ ኤንባሲ የተዘጋጀ የቅርሳቅርስ ውድድር ተካሄደ
ይህ ውድድር ከዩንቨርስቲ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚገኙትን ሴት ተማሪዎች ለማበረታታት
እና ተሰጦአቸውን እንዲያወጡ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ ውድድር ሲሆን
ከአድሀቂ ግቢ የቅርሳ ቅርስ ተማሪ የሆኑ 3 ሴት ተማሪዎች ውድድሩን ለመካፈል ስራቸውን ልከው ውጤቱን በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ የትምህርት ክፍሉ ተጠሪ ገልጸዋል፡፡
ሀገራችን በዚህ ዘርፍ
ያላትን ተሳትፎ እና እንቅስቃሴ ለማሳደግ መነሳት ያለብን እታች ካሉ ክፍሎች መሆን እንዳለበት የትምህርት ክፍሉ ተጠሪ አስታውቀዋል፡፡
በተለይም በዘርፉ ተተኪ ከማፍራት አንፃር እንዲሁም የሴት ተማሪዎቹን አቅም ከማጎልበት እረገድ
ጠቃሚ እና አበረታች እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
No comments:
Post a Comment